Service Times/ የአገልግሎት ጊዜዎች


የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ለመከላከል መንግስት እንዳንሰበሰብ ባወጣው መመርያ መሰረት የእሁድ ጠዋት የቤተክርስቲያ ስብሰባ በቀጥታ ስርጭት ብቻ ይደረጋል። 

የእሁድ ጠዋት አገልግሎት ዘወትር እሁድ፦ 

  • በአማርኛ ከ10:00 -11: 30am
  • በእንግሊዝኛ (English service) 11:45am - 12:00pm

የማለዳ የፀሎት ፕሮግራም ሰኞ፤ ሐሙስ፤ ዓርብ፤ ቅዳሜና እሁድ ከጠዋቱ 6:30 እስከ 8:00 በስልክ ጥሪ የሚደረግ ስለሆነ በተዘጋጀው ስልክ ቁጥርና በመግቢያ ቁጥር በመደወል
መሳተፍ ይቻላል።

የማክሰኞ የጾምና የፀሎት ፕሮግራም ከ11am - 1pm ሲሆን አስቀድሞ በቤተክርስቲያን ቢሮ በመመዝገብና በህንፃ በውስጥ በመገኘት መካፈል ይቻላል።

የሮብ ምሽት የፀሎት ፕሮግራም ከምሽቱ 7pm - 9pm አስቀድሞ በቤተክርስቲያን ቢሮ በመመዝገብና በህንፃ ውስጥ በመገኘት ወይንም በቀጥታ ስርጭት መሳተፍ ይቻላል።ለበለጠ ወቅታዊ የመንግስት ማሳሰብያ ለማወቅ የሚቀጥለውን ማስፈንጠርያ ይጫኑ።     https://www.nhs.uk/conditions/coronavirus-covid-19/ 

የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስትያን አገልግሎቶች እና ስብሰባዎች አስቸኳይ ማስታወቂያ።

 

የኮሮና ቫይረስ በሽታ (COVID-19) በ 2019 ውስጥ የተገኘና ከዚህ በፊት በሰዎች ላይ ያልታየ አዲስ በሽታ ነው።

ሰኞ 16 ማርች 2020 እ.ኤ.አ. በCOVID-19 በተከሰተው የወረርሽኝ በሽታ ቀውስ ምክንያት የዩናይትድ ኪንግደም መንግስትና የህዝብ ጤና ምክር ቤት ሰዎች በብዛት በአንድ ላይ እንዳይሰበሰቡ በማለት ማስጠንቀቂያና ትብብር በመጠየቁ ምክንያት ሁሉንም የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ከዛሬ ጀምሮ ለማቆም የሽማግሌዎች ጉባኤ ከብዙ ውይይትና ምክክር በኃላ ውሳኔ ወስነኗል:: እንደ ቤተክርስቲያን ይህንን ውሳኔ ለመወሰን የቻልነው ነገሩን በቁም ነገርና በጥልቀት አይተን ሲሆን ይህንንም ማድረጋችን ለየያንዳንዳችንና ለሁሉም የህብረተሰብ አባላት ያለብንን የእንክብካቤ ግዴታና የህዝብ ሃላፊነት ለመወጣት ነው።

የመጨረሻዎቹ የመንግስት ጥብቅ ምክሮች ስብሰባዎች እንዳይደረጉ እገዳንና “ማህበራዊ  መራራቅ” አድርጉ የሚል ጥሪን ያካትታል ፡፡

የጤና ፀሀፊው ማት ሃንኮክ ሰኞ ምሽት ላይ በተወካዮች ምክር ቤት በጋራ ለሚኖሩ ጥያቄዎች በበኩላቸው መልስ ሲሰጡ ፣   “በጥልቅ ፀፀትና በጣም እየከበደን የምንመክረው የአምልኮ ቦታዎች ጭምር በዚህ እገዳ ውስጥ ይካተታሉ” ብለዋል ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው እንዳይሰራጭ ለመከላከል እንደመሆኑ መጠን መንግስት ከትንሽም ከትልቅም የቡድን ስብሰባዎች ራቅ እንድንል ጠይቋል ፡፡ በዚህ ወቅታዊ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔርን እንድናገለግለው በተጠራን ሰዎችና ማህበረሰቦች መካከል እንክብካቤና ድጋፍን ማምጣት አለብን ፡፡ ከኢየሱስ ጋር በቅርብ እየተራመድን ፣ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜና ሁኔታ ተያይዘን ከእርሱ ጋር ስንሰራ እንደሚመራንና እንደሚረዳን እርግጠኞች ነን።

ኮሮናቫይረስ ሁላችንም ትኩረት ሰጥተነዋል ፡፡ ይሄ ጥሩ ቢሆንም ነገር ግን ከመደናገጥ ይልቅ በጸሎትና በምልጃ እንዲሁም ከጥንቃቄ ጋር እርምጃ ስንወስድ ይሸነፋል። የሁሉም ደህንነት ለእኛ እጅግ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ልባችንና ጸሎታችን በበሽታ ከተጎዱት ጋር ነው፡፡

ስለዚህም ፕሮግራሞቻችን እንደሚከተለው እንዲካሄዱ ተወስነዋል ፡፡

የመንግስት መመሪያዎችን ለማክበርና የሁሉንም ደህንነት ለመጠበቅ በጣም ጥሩው መንገድ ሆኖ ያገኘነው  የህዝብ አምልኮና የአብሮ ስብሰባዎቻችን ለጊዜው አቁመን ከቤታችን ሆነን የምንሳተፍበትን  የቀጥታ ስርጭት አገልግሎትን መከታተል ነው።

የሰንበት አገልግሎታችን እና ረቡዕ ምሽት የጸሎት ስብሰባ በቤት ውስጥ ሁሉም ሰው ማምለክ ፣ መመልከት እና መሳተፍ እንዲችል በተለመደው በፌስቡክ እና በ YouTube በቀጥታ ፣ ይተላለፋል ፡፡

እሁድ ጠዋት የቀጥታ ስርጭት

ከጠዋቱ 10 - 11:30 am ይተላለፋል

የማክሰኞ የጾምና የፀሎት ፕሮግራም በቤተክርስቲያን ቢሮ በመመዝገብ

ከ11am - 1pm

የረቡዕ ምሽት ፀሎት የቀጥታ ስርጭትና በህንጻ ውስጥ ይደረጋል በቤተክርስቲያን ቢሮ በመመዝገብ የቀጥታ ስርጭትና  

ከምሽቱ 19:00 - 20:00 ይተላለፋል

የቤት ህብረት አንዱ የቤተክርስትያናችን ጥንካሬ ስለሆነ  እርስ በእርስ በማያያዝና በማትጋት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ሁሉ በእግዚአብሔር ጸጋ ለስራው እንዲንቀሳቀስ ያስፈልጋል ፡፡ ስለዚህም ለጸሎትና ለ መፃፍ ቅዱስ ጥናት አብረን ባንሆንም የመገናኛ መንገዱ teleconferencing በኩል እንዲሆን እናበረታታለን ፡፡ የእያንዳንዳችንን ደህንነት በየቀኑ በተመለከተ ሽማግሌዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን መሪዎች ጋር በትብብር ይሰራሉ ​​እናም እንደ አስፈላጊነቱ ጸሎትንና ምክርን ለማቅረብ ይችላሉ።

በፌስቡክና በዩቲዩብ ላይ የሚተላለፉትን በመጠቀም ከቤተክርስቲያናችን ጋር በመፅለይ እንዲቆዩ እናበረታታዎታለን።

ለተጨማሪ መረጃና አገልግሎት በሚከተለው መስመር ሊያገኙን ይችላሉ-

ስልክ ለመደወል:

በኮረና በሽታ ምክንያት በተፈጠሩ የተለያዩ ችግሮች እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ቤተክርስቲያን ለማገዝ ዝግጁ ስለሆነች  በ ስልክ ቁጥር :07379 973679 

ለፀሎት: 07375112886 
በቢሮ ሰዓት : 02072780010 

 በኢሜል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ይላኩ።

 መባ፥ አስራትና ስጦታ በቤተክርስቲያን የባንክ አካውንት ቁጥር መስጠት ትችላላችሁ። እንዲሁም paypal ተጠቅማችሁ ለመስጠት የሚቀጥለውን ተጫኑ።  

መጸለያችንን እና ልባችንን በአንድ ላይ አንድ ማድረጋችንን እንቀጥል ፡፡ እንደ ክርስቲያን የተጠራነው ጥሪ ከአፋጣኝ ማዕበል ባሻገር እንድንመለከት ፣ ጥንካሬን ፣ ተስፋን እና እምነትን በትጋት እንድንፈልግና እንድንበረታይፈልጋል ፡፡


መዝሙር 91

1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።

2 እግዚአብሔርን። አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።

3 እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።

4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።

5 ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥

6 በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።

7 በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

8 በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።

9 አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።

10 ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።

11 በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤

12 እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

13 በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

14 በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።

15 ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።

16 ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።


 

ከመንግስት እና ከህዝብ ጤና አካላት የሚሰጡ ምክሮችን መከታተል እንቀጥላለን እንዲሁም አስፈላጊውን ድረ ገፃችን ላይ አስቀምጠን በየጊዜው እናሻሽለዋለን ፡፡

ለተጎዱት እንድንፀልይና አስፈላጊዉን እርዳታ ማረግ እንድንችል በተቻለ መጠን እባክዎን መረጃን በፍጥነት ያጋሩን።

 

እግዚአብሔር ይባርካችሁ ይጠብቃችሁ።

የሽማግሌዎች ጉባኤ።Church Services and gatherings - ECFCUK announcements:

Coronaviruses are a large family of viruses that cause illness ranging from the common cold to more severe diseases such as Middle East Respiratory Syndrome and Severe Acute Respiratory Syndrome.

Coronavirus disease (COVID-19) is a new strain that was discovered in 2019 and has not been previously identified in humans.

As a result of the latest UK government and Public Health advise regarding the COVID-19 crisis on Monday 16th March 2020, we are taking the decision to suspend all ECFCUK Church services with immediate effect until further notice.

We do not take this decision lightly but do so believing we have a public duty to act responsibly in terms of the duty of care to all members of the community.

The latest advice includes a Government ban on large gatherings and a call for “social distancing”.

Answering questions in the House of Commons on Monday evening, Health Secretary Matt Hancock said: “with the deepest regret and the heaviest of hearts we do include faith groups within the advice”.

In order to prevent the spreading of the virus from person to person, the Government has requested that we must isolate ourselves from group gatherings.

In this current situation, our priorities must be to bring care, support and hope to the people and communities we are called to serve. We are confident that if we walk closely with Jesus, He will lead and direct us to work with Him throughout this difficult time and beyond.

The Coronavirus is causing concern for all of us. A prayer and carefully thoughtful action rather than panic will overcome it. Your safety is extremely important to us and our hearts and prayers go out to those that have been affected.

ECFC UK has decided as follows:

• The best way to protect everyone is to respect government guidelines and stop face to face public worship services and switch to live streaming for all of us to participate from our home.

  • Our Sunday service and Wednesday evening prayer meeting will be live streamed, transmitted, on Facebook and YouTube as usual so that everyone can worship, watch and participate in prayer from home.  

Live stream on Sunday: Between 10:00 a.m. – 11:30a.m.

Live stream on Wednesday prayer: 19:00 - 20:00 (7pm – 8pm)

• Our Home fellowships are one of the ECFCUK strengths and we encourage the fellowships to rise up in this challenging time to care for and follow up on each other. We encourage our home fellowship to meet and pray through teleconferencing.

The Elders will be closely working with Bible study group leaders regarding the wellbeing of our congregation on a daily basis and be able to deliver prayer and advice as necessary.

• We encourage you to stay connected to our church family by clicking on these links http://www.ecfcuk.org/index.php/theme-features-3/layouts-2 and our Facebook page.

You can also contact us as follows: Office hours: 020 7278 0010 on (Monday, Wednesday and Friday between 10 a.m. to 4p.m.)

Emergency Line Regarding Coronavirus (COVID-19) 07379 973679 

Prayer Line 07375112886

or email This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it..

• Let us continue to pray and unite our hearts together. The call to Christian ministry requires of us that we look beyond the immediate storm, finding strength, hope and faith in God. Yet, it also requires that we bring that ‘down the mountain’ to minister to people where they are.

Psalm 91 and Isaiah 26:20,

 

We will continue to monitor and examine advice from the government and Public Health bodies and will update our website, resources and advice as necessary.

Please share information and tell us the affected people so that we can pray and reach out to them as promptly as possible.

 

Time to worship Lord by giving via PayPal or ECFC UK account.

 

Gifts, Tithes and Offerings link:  

 

May Lord bless you